
ሀዋሳ፤ የካቲት 24/2017 (ኢዜአ)፡-የገጠር ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ዘላቂ የልማት ግቦችን ማሳካት የሚያስችል ፕሮግራም ተነድፎ ወደተግባር መገባቱን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታወቀ፡፡
በሲዳማ ክልል የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢኒሼቲቪ ትግበራ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በሃዋሳ ከተማ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር) በዚህ ጊዜ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ በገጠር ያለውን ሀብት፣ ጉልበትና እውቀት መሰረት ያደረገ ኢንዱስትሪ ለማስፋፋት የሚያስችል ፕሮግራም ተቀርጾ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡
ፕሮግራሙ በገጠር ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል ሲሆን ኤክስፖርትንና ተኪ ምርትን በማሳደግ ረገድም ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
በሲዳማ ክልል ሀዋሳና ይርጋለም አካባቢ ያለውን ሰፊ የኢንዱስትሪ ልምድ በገጠር ወረዳዎች በመተግበር ፕሮግራሙን ማሳካትና የሚፈገለውን ውጤት ማምጣት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና በበኩላቸው በገጠር ኢዱስትሪዎችን ለማስፋፋት የተቀረጸውን ሃገራዊ ፕሮግራም መነሻ በማድረግ ክልላዊ ኢንሼቲቪ መቀረጹን ገልጸዋል፡፡
ኢንሼቲቩ በክልሉ ባሉ 30 ወረዳዎች የሚተገበርና የወረዳዎቹን አቅም በመለየት የሚከናወን መሆኑም አስረድተዋል።
በዚህም በየወረዳዎቹ ከሦስት እስከ አምስት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በመፍጠር በበጀት ዓመቱ 104 አዳዲስ የገጠር ኢንዱስትሪዎች ለመገንባት እቅድ ተይዟል ብለዋል፡፡
በክልሉ በተፈጥሮ ሃብትና ግብርና፣ በማዕድንና በእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ ያለውን የግብዓት አቅም ወደ ኢንዱስትሪ ለመቀየር ትኩረት መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡
በክልሉ 8 ኢንሼቲቮችና 68 ፓኬጆች ተቀርጸው የቤተሰብ ብልጽግና ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አሸናፊ ኤሊያስ ናቸው፡፡
በክልል ደረጃ ከተቀረጹ የልማት ፓኬጆች መካከል የኢንዱስትሪው ዘርፍ እንደሚጠቀስ ገልጸው በገጠር ኢንዱስትሪዋችን ለማስፋፋት በየአካባቢው ያለው አቅም ተለይቷል ብለዋል፡፡
በዚህም አመራሩ ሞዴል አርሶ አደሮችን ጨምሮ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራትን በመደገፍ አምራች ኢንዱስሪትውን እንዲቀላቀሉ ማገዝ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካካል የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሰለሞን ዮናስ እንደገለጹት የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ለማስፋፋት የተጀመረው ኢንሼቲቭ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡
እንደ ዞን ቡናን ጨምሮ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በሰብልና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ያሉ አቅሞች መለየታቸውን ጠቁመው፣ ማህበራትንና ሞዴል አርሶ አደሮችን ወደ ኢንዱስትሪው ለማስገባት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚህም በሃገርም ሆነ በክልል ደረጃ ለተቀረጹ ፕሮግራሞች ስኬት በትኩረት እንደሚሰራ ነው ያመለከቱት።
በመድረኩ በሃገርና በክልል ደረጃ የገጠር ኢንዱስትሪላይዜሽንን ለመተግበር በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026