ባሕር ዳር፤ የካቲት 26/2017 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ባለፉት ሰባት ወራት ከ2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የቅባትና የጥራጥሬ ምርት በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ለውጭ ገበያ መቅረቡን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ በተለይም የወጭና ገቢ ምርቶችን ሚዛን ለመጠበቅ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በብዛትና በጥራት ለውጭ ገበያ እየቀረቡ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በአማራ ክልል ባለፉት ሰባት ወራት ከ2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የቅባትና የጥራጥሬ ምርት፤ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ለውጭ ገበያ መቅረቡ ተገልጿል።
በአማራ ክልል የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሰብልና የኢንዱስትሪ ምርቶች ግብይት ዳይሬክተር፤ አቶ ልንገረው አበሻ፤ በበጀት ዓመቱ ከ5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል የቅባትና የጥራጥሬ ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ ግብ መያዙን አስታውሰዋል።
በዚህም መሰረት ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ ከ2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የቅባትና የጥራጥሬ ምርት በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ለውጭ ገበያ ቀርቦ ከ215 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።
ለውጭ ገበያ ከቀረቡት ምርቶች መካከልም የሰሊጥ፣ የማሾ፣ የአኩሪ አተርና የቦሎቄ ምርቶች መሆናቸውን ዘርዝረዋል።
ከገበሬው እስከ ገበያ መዳረሻዎች ጥራቱን በጠበቀ አግባብ ተመርቶ ለገበያ እንዲቀርብ ለማድረግ የተደረገው ጥረት ውጤት ማምጣቱንም ተናግረዋል።
በባለፈው በጀት ዓመት ከክልሉ በምርት ገበያ በኩል ለውጭ ገበያ ከቀረበ 3 ሚሊዮን 910 ሺህ ኩንታል የቅባት እህል 478 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱም ታውቋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025