አርባምንጭ የካቲት 29/2017(ኢዜአ):- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጀመሩ ሥራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ።
በክልሉ የ2017 ግማሽ ዓመት የፓርላማና የክልል ምክር ቤት አባላት ውክልና ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሄዷል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በልማትና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ከመረጧቸው ህዝቦች ጋር ሰሞኑን ውይይት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ከክልሉ አመራር አባላት ጋር የማጠቃለያ መድረክ አካሄደዋል።
በምክር ቤቱ የመንግስት ልማት ድርጅት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንጂነር ስለሺ ኮሬ (ዶ/ር) በክልሉ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።
በተለይ በፌደራልና በክልሉ መንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የጤና እና የትምህርት ልማቶች ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።
የግብርና ግብዓትና ቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የተጀመሩ ተግባራትና የሀገር ውስጥና የውጭ የሥራ ዕድል ፈጠራዎችም እንዲጠናከሩ አሳስበዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ውክልና ሥራ አስተባባሪ አቶ መለሰ መና በበኩላቸው ከመንግስት ሠራተኞች የወርሃዊ ደመወዝ ክፍያ ጋር የሚነሱ ቅሬታዎች እየተፈቱ መምጣታቸውን መገንዘባቸውን ተናግረዋል።
''የህዝብ የመልማት ጥያቄ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል ለተጓተቱ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ምላሽ ለመስጠት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ሊጠናከሩ ይገባል'' ብለዋል።
በተለይም የመንገድ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና የመብራት አገልግሎት ልማት ሥራዎችን በፍትሃዊነት ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ እንዳለም ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ተጠያቂነት ባለውና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወን እንዲሁም የነዳጅ አቅርቦት ችግርና ህገ-ወጥነትን የማስወገዱ ተግባር በትኩረት ሊሠራ ይገባል ብለዋል።
የተሰጡ አስተያየቶች በመቀበል በቀጣይ በሁሉም መስክ የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ይሰራል ያሉት ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ ዶክተር ቦሼ ቦምቤ ናቸው
በተለይም የግብርና ግብአት አቅርቦትና ሜካናይዜሽንን በማስፋፋት፣ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር፣ የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ የተጀመሩ ውጤታማ ጥረቶች ይጠናከራሉ ብለዋል።
የጤና ተቋማት ግንባታ በማፋጠን አገልግሎቱን ለማሳለጥ እንዲሁም የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ህዝቡን ያሳተፈ ንቅናቄ በመፈጠሩ ለውጥ እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።
በክልሉ ባሉ 12 ዞኖች ከህዝቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት እንደሚሠራም ዶክተር ቦሼ ጠቁመዋል።
ለአንድ ቀን በተዘጋጀው መድረክ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የክልል ምክር ቤት አባላት፣ የክልሉ አስፈጻሚ አካላት እና የዞን አፈ-ጉባኤዎች ተሳትፈዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025