ደሴ/ ደብረ ብርሃን ፤ የካቲት 29/2017 (ኢዜአ) ፡- በአማራ ክልል የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ ውጤት እያስገኘ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
''ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ሃሳብ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በክልል ደረጃ ዛሬ በደሴ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) በበዓሉ ላይ እንደገለጹት ያለ ሴቶች ተሳትፎ የሚረጋገጥ ልማት የለም፡፡
በክልሉ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ ያለው ስራ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል።
ዛሬ በደሴ ከተማ ባደረግነው ጉብኝት ሴቶች በግብርና፣ በአገልግሎት፣ በሌማት ቱርፋትና በሌሎችም ውጤታማ ዘርፎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ብርቱካን ሲሳይ በበኩላቸው፤ የሴቶችን ሁለተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማሳደግ ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተደራጅተው ብድር በማግኘት በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በእንሰሳት እርባታ፣ በማድለብና ሌሎች የሥራ ዘርፎች በማሰማራት ሀብት ማፍራት እንዲችሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በዓሉ በሰሜን ሸዋ ዞን በተከበረበት ወቅት የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ገበያ ተስፋ፤ የሰሜን ሸዋ የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ውጤታማ እንደሆነ በመስክ ማጋገጣቸውን ተናግረዋል።
ፓርቲው ሴቶችን በስልጠናና ሌሎች ድጋፎች በማበረታታት ወደ አመራርነት እንዲመጡ መስራቱን ገልጸዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን ሴቶች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራት በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው ያሉት ደግሞ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ ሰርክ አዲስ አታሌ ናቸው።
የዞኑ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ የሮምነሽ ጋሻውጠና በበኩላቸው፤ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ሴቶች ተጠቃሚ ናቸው ብለዋል።
በቡልጋ ከተማ የኢንዱስትሪ በባለቤት ወይዘሮ አቻም የለሽ ተስፋሁን በሰጡት አስተያየት፤ በ240 ሚሊዮን ብር ካፒታል የከፈቱት ፋብሪካ ከ70 ሰዎች በላይ የስራ እድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል።
በደሴ ከተማ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተሰማሩት ወይዘሮ ዚነት ሰይድ፤ በልማት ስራ ተሰማርተው የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ ምርት ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በዝግጅቶቹ ላይ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሮች አመራር አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025