የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የገቢ መሰብሰብ አቅምን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Mar 11, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2017(ኢዜአ)፦ የሀገር ውስጥ ገቢ የመሰብሰብ አቅምን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ኮንፍረንስ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኮንፍረንሱ "የልማት ግቦችን ለመደገፍ የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን ማጎልበት" በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።

የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይኤምኤፍ) እና የአይኤምኤፍ ቀጣናዊ የቴክኒክ ድጋፍ ማዕከል የምስራቅ አፍሪካ ቢሮ(አፍሪታክ) ስብሰባውን በጋራ ያዘጋጁ ተቋማት ናቸው።

በኮንፍረንሱ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎችን ጨምሮ ከ11 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተወከሉ የገቢው ዘርፍ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሚመለከታቸው የገቢና ፋይናንስ ባለሙያዎችና አማካሪዎች እንዲሁም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ይገኛሉ።

የኮንፍንሱ ዋና ዓላማ የልማት ግቦችን መደገፍ የሚያስችልና የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን ለማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ያተኮረ ነው።

ቀጣናዊ ኮንፍረንሱ እስከ መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

ከሁነቱ ጎን ለጎን የተሳታፊዎች የጉብኝት መርሃ ግብር ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.