የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የአማራ ክልልን ግብርና ማሸጋገር ሀገራዊ የብልፅግና ግባችንን ለማሳካት ትልቅ አቅም ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Mar 11, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2017(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልልን ግብርና ማሸጋገር ሀገራዊ የብልፅግና ግባችንን ለማሳካት ትልቅ አቅም ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የክልሉን ግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ በተዘጋጀው የአስር ዓመት የመነሻ ዕቅድ ላይ ከምሁራንና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተናል ብለዋል።


ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በየክልሎቻችን የሚገኙ የግብርና እምቅ ፀጋዎችን፣ ሀገር በቀል ፖሊሲና አቅሞቻችንን አሟጠን መጠቀም ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ይህንን እምቅ ፀጋ ለይቶ ለልማት በማዋል እና የክልሉን የመልማት አቅም በማባዛት፣ ሀገርን ከድህነት ለማላቀቅ ትጋት፣ ትኩረትና መናበብን ይፈልጋል ነው ያሉት።

በመሆኑም ዕቅዱን ከሀገራዊ ግቦቻችን ጋር በተናበበ መልኩ ለማስፈጸም የሥራ ባህልና የአመለካከት ለውጥ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም በተነሳሽነትና በቁጭት ሊሠራ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.