ደሴ፤ መጋቢት 2/2017(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የመንገድ መሰረተ ልማቶችን የማሻሻል ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ መንገድ ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ጋሻው አወቀ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ የሚገኙ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን የማሻሻል ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
በክልሉ ከአንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የ95 ድልድዮች ግንባታ መጀመሩን ገልጸው በክልሉ ዞኖችን፣ ወረዳዎችንና ቀበሌዎችን ለማገናኘት ከዚህ በፊት በገጠር ተደራሽነት ተሰርተው የነበሩ መንገዶችን እንደሚያሻሽሉ አስረድተዋል።
አዲስ በሚሰሩና እየተሰሩ በሚገኙ መንገዶች መካከል በክልሉ መንግስትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚገነቡት እነዚህ ድልድዮች ቀደም ሲል ያጋጥሙ የነበሩ የመንገድ ተደራሽነት ችግሮችን እንደሚያቃልሉም ጠቁመዋል።
መንገዶቹ ክረምት ከበጋ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ታቅዶ የሚገነቡት ድልድዮች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ክትትል እንደሚደረግባቸውም አስረድተዋል።
ከሚገነቡት ውስጥም 24 ተንጠልጣይ ድልድዮች እንደሆኑ ጠቅሰው፤ ሁሉም ድልድዮች በተያዘው የበጀት ዓመት አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት መታቀዱን አመልክተዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን መንገድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ሐሰን በበኩላቸው፤ በዞኑ የሶስት ድልድዮች ግንባታ መጀመሩንና ከመካከላቸውም ሁለቱ ተንጠልጣይ እንደሆኑ ገልጸዋል።
በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት እንዲጠናቀቁ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025