አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017(ኢዜአ)፡- 57ኛው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የፋይናንስ፣ምጣኔ ሃብትና ፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ በባለሙያዎች ደረጃ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል።
ጉባዔው “ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን ማፋጠን፤ አፈጻጸሙን የሚያልቁ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎችን መቀየስ” በሚል መሪ ሀሳብ ይከናወናል።
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ የእስከ አሁን አፈጻጸም እና ቀጣይ ስራዎች የጉባዔው ዋንኛ አጀንዳ መሆኑን ኢዜአ ከኢሲኤ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዲጂታላይዜሽን፣ የምግብ ዋስትና እና የኢነርጂ ትራንስፎርሜሽን ሌሎች የጉባዔው የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
57ኛው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) የፋይናንስ፣ ምጣኔ ሃብትና ፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ በባለሙያዎች ደረጃ ከመጋቢት 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
ጉባዔው በሚኒስትሮች ደረጃ መጋቢት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን በጉባዔው መሪ ሀሳብ ላይ ከፍተኛ የፖሊሲ ምክክር መድረክ ያደርጋሉ።
በተጨማሪም ከጉባዔው ጋር የተጓዳኙ የተለያዩ ሁነቶች እንደሚደረጉም ኢሲኤ አስታውቋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025