የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀ እና የጋራ ስራ ማከናወን ይገባል - የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር

Mar 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 3/2017 (ኢዜአ)፦ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የተቀናጀ እና የጋራ ስራ ማከናወን እንደሚገባ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።

የዘላቂ የልማት ግቦች የቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በረከት ፍስሃፅዮን ኢትዮጵያ ለዘላቂ ልማት ግቦች ውጤታማነት በቁርጠኝነት እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ በረከት ፍስሃፅዮን ኢትዮጵያ የዘላቂ የልማት ግቦች ሁሉን ባካተተ መንገድና በዘላቂነት ውጤታማ ሆኖ እንዲተገበር በቁርጠኝነት እየሰራች እንደምትገኝ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የቴክኒካል ኮሚቴው አባላት ከፌዴራል ሚኒስቴር አስፈፃሚ የመንግስት ተቋማት፣ ከልማት አጋሮች፣ ከሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከግል ዘርፍ የተውጣጣ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.