ዲላ፤መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴው ግድብ ግንባታ ከ179 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ የሕዳሴው ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።
በክልሉ በቀጣይ ህዝባዊ ተሳትፎን በማጠናከር ገቢን ለማሳደግ በየደረጃው የንቅናቄ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑም ተመላክቷል።
የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ዘርፉ አጥናፉ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የክልሉ ህዝብ ለሕዳሴው ግድብ የቦንድ ግዥ በመፈጸም ድጋፉን እያጠናከረና አሻራውን እያሳረፈ ይገኛል ።
በተለይ የሕዳሴው ግድብ ዋንጫ ወደ ክልሉ መምጣትን ተከትሎ በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ዋንጫውን በማዘዋወር የገቢ ማሰባሰብ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በተያዘው ዓመት ያለፉት ስድስት ወራት በቦንድ ግዥና በስጦታ ከ179 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
በክልሉ ዘንድሮ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ነው" ያሉት ሃላፊው በቀጣይ ወራት የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር ዕቅዱን ለማሳካት በየደረጃው የንቅናቄ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአንድነታችን ማሳያና የዛሬው ትውልዱ አድዋ ነው ያሉት አቶ ዘርፉ፣ ህብረተሰቡ በቦንድ ግዥና በተለያየ መንገድ ሲያደርገው የነበረውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025