የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የህብረት ስራ ማህበራት አሰራራቸውን ለማዘመን በዘርፉ የተጀመረውን ሪፎርም መተግበር ይገባቸዋል - የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን

Mar 15, 2025

IDOPRESS

አዳማ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፡- የህብረት ስራ ማህበራት አሰራራቸውን በማዘመን የፋይናንስ አቅማቸው እንዲጎለብት በዘርፉ የተጀመረውን ሪፎርም መተግበር እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ገለጸ።

የፌዴራል፤ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የህብረት ስራ ሪፎርም ስራ አፈፃፀም፤ የአሰራርና አገልግሎት አሰጣጥ ፍኖተ ካርታና የፖሊሲ ዝግጅት ሂደት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።


በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ሹጉጤ እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ የህብረት ስራ ማህበራት የመወዳደር አቅማቸውን ለማሳደግና በገበያ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ የተቀናጀ ሪፎርም እያከናወነ ይገኛል።

ማህበራቱ የዘመነ አሰራርና ቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅም እንዲፈጥሩ፤ የፋይናንስና ኦዲት አሰራራቸው ዲጂታላይዝድ እንዲሆን ሪፎርሙ አጋዥ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይ ከተለምዷዊ አሰራር እንዲወጡ የአሰራር፤ የአመራር፤ የቴክኖሎጂና የአገልግሎት አሰጣጥ መዳረሻ አመላካች ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።

በእስካሁኑ ሂደትም በግብይት አፈፃፀም፤ በገንዘብ ቁጠባና ቡድር ስርጭት፤ በካፒታል ዕድገት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ነው ያሉት።


ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ልዕልት ግደይ በበኩላቸው ሪፎርሙ የአደረጃጀት፤ የአሰራር፤ የዕውቀትና ክህሎትን እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን መሰረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ህብረት ስራ ማህበራት የተናበበ የአሰራር ስርዓት በመፍጠር የግብርና ምርትን ለሸማቾች በቀጥታ እንዲያቀርቡ አቅም የፈጠረ ነው ብለዋል።

አዳዲስ አሰራር፤ ህጎችና ደንቦችን በማሻሻል በተለይ የህብረት ስራ ማህበራት የአሰራርና የፋይናንስ አቅምን በማጎልበት ችግሮቻቸውን በውስጥ አቅማቸው እንዲቀርፉ በሪፎርሙ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።


የአማራ ክልል ህብረት ስራ ባለስልጣን ሃላፊ አቶ ጌትነት አማረ እንደገለፁት ሪፎርሙን ውጤታማ ለማድረግ የማህበራት ደረጃዎችን ከመለየት ባለፈ ስድስት መመሪያዎችና ደንቦችን በማዘጋጀት ለአባላቱ ግንዛቤ በመስጠት ወደ ስራ ተገብቷል።

የማህበራት የፋይናንስና የመወዳደር አቅምን ለመገንባት ውስን አቅም ያላቸው ማህበራትን ለማዋሃድ እየተሰራ ሲሆን በተለይ የአባላቱን ጥቅም ማረጋገጥ ያልቻሉትን በሪፎርሙ መሰረት ፍቃዳቸውን የመሰረዝ ስራዎች እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።


በተመሳሳይ ደረጃውን ያሟሉ ማህበራት በሰለጠነ የሰው ሃይልና በቴክኖሎጂ በማደራጀት አዳዲስ አሰራሮችን ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የማህበራት የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር፤ የሂሳብና ኦዲት፤ አገልግሎቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲመሩና በዘርፉ የተናበበ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.