ጎንደር፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፡- በጎንደር ከተማ በዘመናዊ የዶሮ እርባታ ሥራ ለሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች በ60 ሚሊዮን ብር የ10 ሼዶች ግንባታ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ።
የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በከተማው እየተከናወኑ ያሉ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝት ወቅት የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው እንደገለጹት፣ ከተማ አስተዳደሩ በመደበው 60 ሚሊዮን ብር የ10 ሼዶች ግንባታ ሥራ እየተከናወነ ነው።
ሼዶቹ በከተማው በዘመናዊ የዶሮ እርባታ ሥራ ለሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚተላለፉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
በክላስተር በተደራጀ አግባብ በሚከናወነው የዶሮ እርባታ ሥራም አካል ጉዳተኞች በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አመልክተዋል።
ከፍተኛ አመራሩ ከሌማት ትሩፋት እንቅስቃሴ በተጨማሪ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክረምቱ ወራት የሚተከሉ ችግኞች ዝግጅትንም የጎበኘ ሲሆን የከተማውን የኮሪደር ልማት የሥራ እንቅስቃሴን እንደሚመለከትም ታውቋል።
ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የፍራፍሬ ችግኞች የማፍላትና በንብ ማነብ ሥራ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትም የጉብኝቱ አካል ናቸው።
በጉብኝቱ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር)፣ የርዕሰ መስተዳድሩ የመሠረተ ልማት አማካሪ አቶ ደሴ አሰሜ እንዲሁም የክልሉ መንገዶች ቢሮ ሃላፊ ጋሻው አወቀ(ዶ/ር) ተገኝተዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025