የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

Mar 17, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2017(ኢዜአ)፡- የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 57ኛው አህጉራዊ የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ፣ የአፍሪካ አሕጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ፣ ሚኒስትሮች፣ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጉባኤው “የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን የሚያፋጥኑ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን መቀየስ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ የአፈጻጸም ሂደትና ቀጣይ ተግባራት ላይ በመምከር አቅጣጫ ማስቀመጥ የጉባኤው ዋነኛ አጀንዳ መሆኑም ተገልጿል።

ጉባኤው በባለሙያዎች ደረጃ ከመጋቢት 3-5/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት መካሄዱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.