አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የዓለም ንብ ቀንና የዓለም አቀፍ የምግብ ስርዓት ሽግግር አውደ ጥናትን ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት እያደረገች እንደምትገኝ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት(ፋኦ) ረዳት ዋና ዳይሬክተርና የአፍሪካ ቀጣናዊ ተወካይ አበበ ኃይለ ገብርኤል እና ከድርጅቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ፋራይ ዚሙድዚን ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ኢትዮጵያ ዘንድሮ በምታስተናግደው ሁለተኛውን የዓለም የንብ ቀንና ዓለም አቀፍ የምግብ ስርዓት ሽግግር አውደ ጥናት እንዲሁም የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ እየተሰሩ ባሉ ኢኒሼቲቮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
የዓለም የንብ ቀንና ዓለም አቀፍ የምግብ ስርዓት ሽግግር አውደ ጥናትን ለማካሄድ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
የዓለም የንብ ቀን ዘንድሮ ከግንቦት 12 እስከ 14 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲሁም ዓለም አቀፍ የምግብ ስርዓት ሽግግር አውደ ጥናት ደግሞ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳሉ፡፡
በሁለቱ ዝግጅቶች እና የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ እየተሰሩ ባሉ ኢንሼቲቮች ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025