አዳማ ፤መጋቢት 9/2017 (ኢዜአ) ፡-የአዳማ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችን ስራ ፈጠራ ለማበረታታት የሚያስችል የንግድ ስራ አመራርና የሂሳብ አያያዝ ክህሎት ስልጠና መስጠቱን ገለፀ።
የከተማ አስተዳደሩ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የስራ መስኮች ከተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችና ማህበራት ጋር በብድር አቅርቦትና የአሰራር ማነቆዎችን መፍታት ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ አድርጓል።
የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ በወቅቱ እንደገለፁት የከተማው አስተዳደር የወጣቶችና የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስትራቴጂ ቀርጾ እየሰራ ነው።
በዚህም የግብርና ማኑፋክቸሪንግ ኢንሺዬቲቮችን በመቅረጽ ስራ አጥነትን ለመቅረፍና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በክህሎት የዳበረ አምራች ሃይል ለመገንባት መስራቱን ገልጸዋል።
በተለይም ወጣቶች ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የንግድ ስራ አመራር፣ የሂሳብ አያያዝ እና የፋይናንስ አስተዳደር የክህሎት ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመዋል።
አስተዳደሩ የወጣቶችን የቁጠባ ባህል በማዳበርና የፋይናንስ ማነቆዎችን በመፍታት በማህበራት ተደራጅተው በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የማምረቻና የመሸጫ ማዕከላትን ገንብቶ እያስተላለፈ መሆኑን አንስተዋል።
በተጨማሪም ከሲንቄ ባንክ ጋር በመተባበር በማህበር ተደራጅተው ሀብት ያፈሩ ወጣቶች ወደ ኢንቨስትመንት እንዲሸጋገሩ ሁኔታዎችን እያመቻቸ መሆኑንም አቶ ሃይሉ አመልክተዋል።
በሌላ በኩልም ብድርን ከማሰራጨት ባለፈ ጊዜያቸውን የጨረሱ ብድሮችን በወቅቱ ለማስመለስ ጥረት መደረጉንም ከንቲባው አስረድተዋል።
የአዳማ ከተማ የስራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ጠይብ በበኩላቸው ወደ ስራ ለሚገቡ ኢንተርፕራይዞች የክህሎት ስልጠናና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ ውጤታማ እንዲሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ ነው ብለዋል።
የቁጠባ ባህል እንዲዳብር ከመሰራቱም ባለፈ የመነሻ ካፒታል እጥረትን ለመቅረፍ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ለመስጠት መመቻቸቱን ተናግረዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም 2 ሺህ 347 ማህበራት ተደራጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመው ቀደም ሲል ለማህበራቱ በብድር ተሰጥቶ የነበረ 3 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ጠቅሰዋል።
መንግስት የመሸጫና የማምረቻ ማዕከላትን በመገንባት በ10 ዓመት ውል ለማህበራቱ ማስተላለፉንም አመልክተዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025