የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

5ኛው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ ተጠናቀቀ

Mar 20, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2017(ኢዜአ)፦ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ሲካሔድ የቆየው 5ኛው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት የሥራ ቡድን ስብሰባ ተጠናቋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው 5ኛው የሀገራችን የአለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል ሲሉ አስፍረዋል።

በተለያዩ የድርድር ነጥቦች ዙሪያ ከ110 በላይ ጥያቄዎችን በመቀበል ውጤታማ ድርድር ያካሄደው የድርድር ቡድናችን ማምሻውን ድርድሩን አጠናቅቋል ሲሉም ገልጸዋል።


የሚቀጥለው ስድስተኛው የሥራ ቡድን ስብሰባም በያዝነው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ እንዲካሄድ ከስምምነት ደርሰናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2018 ካሜሩን ላይ በሚካሄደው 14ኛው የዓለም ንግድ ሚኒስትሮች ስብሰባ፤ የዓለም ንግድ ቤተሰብን እንድትቀላቀል ሁላችንም የራሳችንን የቤት ሥራ ለመሥራት ተስማምተን ድርድራችንን ቋጭተናል ብለዋል።

በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናትም ቀሪ የሁለትዮሽ ድርድሮችን ጨምሮ ከጽሕፈት ቤቱ ጋር የሚደረጉ ውይይቶች እንደሚኖሩም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.