አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2017(ኢዜአ):- የሩሲያ ኩባንያዎች በብሪክስ የጋራ ፕሮጀክቶች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጥሪ አቅርበዋል።
ፑቲን በሩሲያ የኢንዱስትዎች እና የስራ ፈጣሪዎች ህብረት ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር የሩሲያ የንግድ ማህበረሰብ በብሪክስ ፕሮጀክቶች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ቭላድሚር ፑቲን የቢብሪክስ ሀገራት በአውሮፓዊያኑ 2024 የ4 ነጥብ 9 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገባቸውን አውስተዋል።
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በቀጣይ አስርት ዓመታት የሚኖረው የዕድገት መጠን የተረጋጋ ሆኖ እንደሚቀጥል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
የሩሲያ የንግድ ማህበረሰብ ከብሪክስ አባል ሀገራት አጋሮች እና ቀጣይ አባል ከሚሆኑ ሀገራት ጋር የጋራ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የተሻለ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሩሲያ ከብሪክስ አጋሮች ጋር በኢነርጂ፣ ኢንዱስትሪ፣ ፋይናንስ እና ሌሎች ዘርፎች በትብብር እየሰራች እንደምትገኝ የብሪክስ ቲቪ ዘገባ ያመለክታል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025