አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2017(ኢዜአ)፡- ባለፉት ስምንት ወራት ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
በማብራሪያቸውም መንግሥት ባለፉት ስምንት ወራት በትኩረት ከሰራባቸው ዘርፎች አንዱ የስራ ዕድል ፈጠራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በሀገር ውስጥ ወደ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዜጎች የስራ ድል እንደተፈጠረላቸው ገልጸዋል።
በውጭ ሀገር የስራ ስምሪትም ከ300 ሺህ በላይ ዜጎች ስራ ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።
እንዲሁም በርቀት የሥራ ዕድል አማካይነት ከ45 ሺህ በላይ ያላነሱ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ሆነው ለውጭ ሀገር ኩባንያዎች እየሰሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
በድምሩ ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የስራ እድል ማግኘታቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
በከተማ እና በገጠር የኮሪደር ስራዎች እና ልዩ ልዩ ኢኒሼቲቮች ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩንም ነው የገለጹት።
በቀጣይም የሥራ ዕድል ፈጠራን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ በማመላከት።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025