አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2017(ኢዜአ)፦ ሴቶች በሳይንስ ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ የግንባር ቀደምትነት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ገለጹ።
የኢትዮጵያ ሴቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማህበር (SEWIST) 6ኛ ዓመታዊ ጉባኤ ተካሂዷል።
ጉባኤው የተካሄደው "የወደፊቱን የሚመሩ ሴቶች፤ የሴት ተመራማሪዎችን በሳይንስ፣በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ማብቃት" በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
የማህበሩ ጉባዔ ሴቶችን በሳይንስ፣ቴክኖሎጂ ፣ፈጠራና ምርምር እድገት ያላቸው ሚና፣ ያሉ እድሎች እና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ነው።
ሚኒስትር ዴኤታው በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ሴቶች በሳይንሳዊ ግኝቶች፣ በቴክኖሎጂ እድገት እና በፈጠራ መፍትሄዎች ግንባር ቀደም ሚና ሊወጡ ይገባል።
በሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ /STEM/ ዘርፎች የሴት ምሁራን ሚና ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መፍትሄ ለማምጣት ሴቶችን ያሳተፈ ስራ ማከናወን እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።
ማህበሩ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራም አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማህበር ፕሬዝዳንት ሄለን ንጉሤ(ዶ/ር ) ኢትዮጵያ በሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን በርካታ ስራዎች እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
በዘርፎቹ የተሟላ ውጤት ለማምጣት የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም በሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግና ሒሳብ /STEM/ ዘርፎች ያላቸውን አቅም መጠቀም እንደሚገባ አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ማህበር በ2014 ዓ.ም የተቋቋመ እና በሳይንስ ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ሚኒስቴሩ በመረጃው አመልክቷል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025