አዲስ አበባ፤መጋቢት 18/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትሕ ቋሚ ጉዳዮች ኮሚቴ ገለፀ።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በኢንስቲትዩቱ የመስክ ምልከታ አድርገዋል።
ኢንስቲትዩቱ ኢትዮጵያን ዓለም ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን በምልከታቸው ማረጋገጣቸውንም ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ምርምሮችን በማከናወንና ቴክኖሎጂዎችን በማልማት ለተቋማት ግንባታ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑንም አባላቱ ተናግረዋል።
ሀገርን የሚጠቅሙና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባውም ነው ያሳሰቡት።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ እፀገነት መንግስቱ፥ ሀገራዊ ሪፎርሙ ትኩረት ካደረገባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ የተቋም ግንባታ መሆኑን አንስተዋል።
ለተቋም ግንባታ መሳካት ቴክኖሎጂን ማዘመን ወሳኝ እንደሆነ ጠቅሰው፥ ቴክኖሎጂ አገልግሎትን ለማቀላጠፍና ምርታማነትን ለማሳደግ እንደሚያስችል ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ፈጠራ እና ፍጥነት ላይ እያከናወነ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን በመስክ ምልከታ መገንዘባቸውን ተናግረዋል።
ኢንስቲትዩቱ በጤና፣ግብርናና ሌሎች ዘርፎች እንዲሁም የአገር ደህንነትን ለመጠበቅ የሚያስችሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል።
ችግር ፈቺ ምርምሮችን እንዲሁም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ።
የለሙ ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ እያከናወነ ያለው ተግባር የሚበረታታ እንደሆነ በማንሳት ተደራሽነቱን ለማስፋት ቋሚ ኮሚቴው ድጋፍና ክትትሉን እንደሚያጠናክር አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፥ ኢንስቲትዩቱ ለትራንስፖርት፣ ጤና፣ ግብርና እና ሌሎች ዘርፎች የሚጠቅሙ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓቶችን በማልማት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢንስቲትዩቱ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከተለያዩ የግል፣የመንግስት እንዲሁም የውጭ ሀገር ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ነው ብለዋል።
በርካታ ምርምሮችን በማካሄድ በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ማሳተም መቻሉንም ነው የተናገሩት።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025