አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2017(ኢዜአ)፡- በውጭ ምንዛሬ ጨረታው አንድ ዶላር በአማካይ 131 ነጥብ 7 ብር መሸጡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለፀ።
ባንኩ ዛሬ ያደረገውን የ50 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።
አንድ ዶላር በአማካይ በ131 ነጥብ 7 ብር መሸጡንና በጨረታው ላይ የተሳተፉ 12 ባንኮች የውጭ ምንዛሬውን መውሳዳቸውን ገልጿል።
ብሔራዊ ባንክ እያደገ የመጣውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ በቀጣይ ወራት በመደበኛነት በየሁለት ሳምንቱ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታዎችን ለማካሄድ መወሰኑን አስታውቋል።
በዚሁ መሰረት ባንኩ ቀጣይ ጨረታ የሚያካሂድበት ቀን እና ሰዓት ጨረታው ከመካሄዱ ከአንድ ቀን በፊት አስቀድሞ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል።
ጨረታው በማዕከላዊ ባንክ እየተከማቸ ካለው የውጭ ምንዛሪ የተወሰነውን መጠን ለግሉ ዘርፍ ለማቅረብና የባንኩን የገንዘብ ፖሊሲ ዓላማ ለማሳካት እንደሚረዳ ተገልጿል።
በተጨማሪም ጨረታው የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና ሪፎርሙ ከተጀመረ ወዲህ መሻሻል እያሳየ የመጣውን የውጭ ክፍያ ሚዛን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚረዳም ነው ባንኩ የገለጸው።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025