አዲስ አበባ፤መጋቢት 24/2017 (ኢዜአ)፦የጉምሩክ ኮሚሽን ባለፉት የለውጥ ዓመታት የሪፎርም ስራዎችን በማከናወን ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚችልበትን አቅም መፍጠሩን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቀበታ ገለጹ።
"ትናንት፣ዛሬና ነገ ለኢትጵያ ልዕልና "በሚል መሪ ሃሳብ ባለፉት የለውጥ ዓመታት እንደ ሀገር በተገኙ ስኬቶችና በቀጣይ የቤት ስራዎች ዙሪያ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች ምክክር አድርገዋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቀበታ፥ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በፖለቲካዊ ፤በኢኮኖሚ፣ በተቋማት የሪፎርም ስራዎች እና በዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
በአገሪቱ ለጉምሪክ አሰራር ማነቆ የነበሩ ህጎችን በማሻሻል አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣሙ ምቹ መደላድል መፈጠሩንም ገልጸዋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት የአሰራር ስርአቱን ለማዘመን በርካታ የሪፎርም ስራዎችን ማከናወኑን አስታውሰው፥ ይህም ኮሚሽኑ ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚችልበትን አቅም እንደፈጠረለት ጠቅሰዋል።
ከለውጡ በፊት ኮሚሽኑ በተለያዩ እቃዎች ላይ ተገቢውን ዋጋ በመተመን ተገቢውን ቀረጥና ታክስ ከመሰብሰብ አኳያ ክፍተት ይታይበት እንደነበር ተናግረዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት ኮሚሽኑ አሰራሮቹን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ በመቻሉ ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ገቢ የመሰብሰብ አቅሙን ማሳደግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
ኮሚሽኑ በራስ አቅም ቴክኖሎጂዎችን በማበልጸግ ሀገሪቱ ከውጭ በምታስገባቸው እቃዎች ላይ ተገቢውን ቀረጥና ታክስ መተመን የሚያስችል አቅም መፍጠሩን አስታውቀዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ኮሚሽኑ ያደረጋቸው የሪፎርም ማሻሻያዎች በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋ እንዲሆኑ አስችሏል ብለዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025