ደብረብርሀን ፤መጋቢት 26/ 2017(ኢዜአ) ፡-የደብረ ብርሃን ወጣቶች የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን በማዳበር ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው የከተማው አስተዳደር ገለጸ።
የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ ሶስት ዓመታት 12 ሺህ ወጣቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማሰልጠን እየሰራ መሆኑም ተመላክቷል።
ከተማ አስተዳደሩ ከኪያሜድ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር "ዲጂታል ቴክኖሎጂ ለትምህርት ጥራት ውጤታማነት ያለው አስተዋጽኦ" በሚል መሪ ሃሳብ በኮደርስ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።
ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ እንዳሉት ወጣቶች አዳዲስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ራሳቸውንና አገራቸውን ሊጠቅሙ ይገባል።
በዚህም የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ ሶስት ዓመታት 12 ሺህ ወጣቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማሰልጠን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በዚህ ዓመት የመንግስት ሰራተኞችን ጨምሮ ሶስት ሺህ ሰዎችን ለማሰልጠን ታቅዶ እስካሁን ከ1 ሺህ 700 በላይ ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ተናግረዋል።
የተጀመረውን ስልጠና ለማጠናከርም የኪያሜድ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ መድረክ በማዘጋጀት ወጣቶችን ለማንቃት እያደረገ ያለው ጥረት የሚመሰገን ነው ብለዋል።
የኪያሜድ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ዲን አቶ መርሻ አሰፋ እንዳሉት መድረኩ ተማሪዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ በማተኮር ራሳቸውን ለማብቃት እንዲችሉ ለማድረግ ነው።
በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ያገኘነው ስልጠና አዳዲስ መተግበሪያዎችን በማበልጸግና በመጠቀም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሀገርን ተወዳዳሪ ለማድረግ የበኩሉን እንደሚወጣ የገለጸው ደግሞ ተማሪ ሲሳይ ማሞ ነው።
ሌላው የስልጠናው ተሳታፊ ተማሪ ኤልያስ አላዩ በበኩሉ የኮደርስ ስልጠናው ለትምህርቱ ውጤታማነት አጋዥ መሆኑን አስረድቷል።
በስልጠናው ላይም የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025