በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተሰማርተው ተጠቃሚ የሆኑ የምስራቅ ሀረርጌ አርሶ አደሮች
አርሶ አደር ዙቤራ አህመድ ይባላሉ። በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ ከ2010 ዓም ጀምሮ በአትክልትና ፍራፍሬ ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆናችውን ይገልጻሉ።
በዚህም ፓፓያ፣ ማንጎ፣ ድንች፣ ጥቅል ጎመን እና ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬዎችን በስፋት በማምረት ከራሳቸው አልፎ ለገበያ እያቀረቡ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በዚህ ዓመት ከአንድ ሄክታር መሬት ላይ ከደረሰው የፓፓያ ምርት 25 ሺህ ብር ማግኘታቸውን ጠቁመው፤ አሁንም ለመሰብሰብ የደረሰ ምርት መኖሩን ይናገራሉ።
ባስመዘገቡት ውጤትም በክልል ደረጃ ከሁለት ጊዜ በላይ እውቅናና ሽልማት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
በዚህ ስራቸውም መካከለኛ ባለሀብት መሸጋገራቸውን ገልጸው፤ በስራቸው ለ25 ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር መቻላቸውን ተናግረው፤ በቀጣይ የአትክልት ምርትን በማቀነባበር ለተጠቃሚዎች ማድረስ የሚያስችል ግንባታ እያካሄዱ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዞኑ የኮምቦልቻ አርሶ አደር ኢብራሂም አሊ በአትክልት ልማት በመሰማራት ጥሩ ውጤት እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል።
የኮምቦልቻ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጀማል ጃቢር (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደገለጹት፤ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራዎች ተከናውነዋል።
በወረዳው በሌማት ትሩፋት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በሌሎች የልማት ስራዎች አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸው፤ በመስኖ ልማት ከ7 ሺህ 400 በላይ ሄክታር መሬት በአትክልትና ፍራፍሬ እየለማ መሆኑን ጠቁመዋል።
በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሚስኪ መሀመድ በበኩላቸው በዞኑ የመሬቱ አቀማመጥ ለእርሻ የማይመች በመሆኑ ያለውን ሃብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
በዚህም የዞኑ አርሶ አደሮችን በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሰማሩ በማድረግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በዚህም እንደየ አካባቢው የአየር ሁኔታ ሙዝና አቮካዶን ጨምሮ በሌሎች የፍራፍሬ ኢኒሼቲቭ እየተተገበረ መሆኑን ጠቁመዋል።
የክልሉ መንግስት ለኢኒሼቲቩ በሰጠው ትኩረት ለዞኑ ለዘር የሚሆኑ የፍራፍሬ ተክል ችግኞችን ለአርሶ አደሮች ተደራሽ በማድረግ እያስፋፋ መሆኑንም ተናግረዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025