አዲስ አበባ፤መጋቢት 28/2017(ኢዜአ):-ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን የልማት እንቅስቃሴ መነሳሳት እንደፈጠረባቸው ኢዜአ ያነጋገራቸው የአፍሪካ አገራት ሚኒስትሮች ገለጹ።
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያከናወነቻቸው የልማት ተግባራት የበርካታ አገራትን ቀልብ ስቧል።
ለዚህ አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናና የዓለምአቀፍ ተቋማት መቀመጫነቷን በሚመጥን መልኩ ልማቷ እየተፋጠነ መምጣቱ በዋቢነትም ይጠቅሳሉ።
አዲስ አበባ እያሳየች ያለው ፈጣን ዕድገት የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማዕከልነቷ እንዲጨምር እያደረገም ነው።
ከተማዋ ለዓለምአቀፍና አህጉራዊ ስብሰባዎችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተመራጭ ከመሆን ባለፈ የበርካታ ጎብኝዎችንም ቀልብ እየሳበች ነው።
የፓን አፍሪካ ወጣት አመራሮች ጉባኤ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የተገኙት የማሊ፣የጋምቢያና የብሩንዲ የወጣቶች፣ ስፖርትና ባህል ሚኒስትሮች ይህንኑ ነው የሚመሰክሩት።
የማሊ ወጣቶች፣ ስፖርትና ዜግነት ጉዳዮች ሚኒስትር አብዶል ቃሲም በወቅቱ እንደገለጹት፥ ኢትየጵያ ሁሉንም ያሳተፈ የልማት ስራ ማከናወኗ ውጤታማ አድርጓታል።
ብዙሃኑን ያሳተፈ የልማት እንቅስቃሴ ውጤቱ ያማረ እንደሚሆን ከኢትዮጵያ ልምድ መውሰድ እንደሚቻልም ነው ያነሱት።
የጋምቢያ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ባርይ ባጄ ከአስር ዓመት በፊት በሚያውቋት አዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ መደነቃቸውን ይገልጻሉ።
አገራቸውን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ከአዲስ አበባ ልማት የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ልምድ የመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል።
የቡሩንዲ የምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ጉዳዮች ፤ወጣቶች ስፖርትና ባህል ሚኒስትር ገርቫይስ አምብ አባይሆ፤ የአገራቸውን ወጣቶች ወደ አዲስ አበባ አምጥተው የማስጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው ነው የገለጹት።
በጉባዔው ለመሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ናሚቢያዊቷ ሻና ግሮዚ አዲስ አበባ በምናብ ከምትታስበው በላይ መሆኗን ገልጻለች።
የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ ውበት ጥበብ በተላበሰ መሰረተ ልማት የበለጠ መጉላቱን በማንሳት።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025