አዲስ አበባ፤መጋቢት 28/2017(ኢዜአ):-በሌማት ትሩፋት መርሃግብር በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የስራ ዘርፎች በመሳተፍ ተጠቃሚ በመሆን ላይ እንደሚገኙ በመርሃ ግብሩ የተሳተፉ የሐረሪ ክልል ወጣቶች ተናገሩ፡፡
ወጣት ረመዳን ሙስጠፋ፥ በሐረሪ ክልል የዲሬጠያራ ወረዳ ነዋሪ ነው፣ ከኮሌጅ በነርሲንግ ከተመረቀ በኋላ ለረጅም ጊዜ ስራ ሳያገኝ መቆቱን ይናገራል።
ለረጅም ዓመታት በስራ አጥነት የቆየው ረመዳን ስራ በማጣቱ ጊዜውን ያለ አግባብ ሲያሳልፍ እንደቆየ ይገልጻል።
በአሁኑ ወቅት የክልሉ መንግሥት ባመቻቸላቸው ዕድል በመጠቀም 2016 ዓ.ም ከተመረቁ 13 ጎደኞቹ ጋር በመሆን በማህበር ተደራጅቶ በዶሮ እርባታ ተሰማራ።
በመርሐ ግብሩ መሳተፍ መጀመሩ ከተለያዩ ሱሶች መላቀቅ እንደቻለ የገለጸው ወጣቱ፤ ይህም በህይወቱ ትልቅ ለውጥ እንዳመጣለት ተናግሯል፡፡
ማህበራቸው ሦስት ሺህ ዶሮዎችን ያረባል፤ በቀንም ሁለት ሺህ እንቁላል እንደሚያገኙ ነው የሚገልጸው።
ሌላው የማህበሩ አባል ወጣት ፈታ ሱፊያን በበኩሉ፥ በአካውንቲንግ ከተመረቀ በኋላ ስራ ሳያገኝ መቆየቱን ያስታውሳል። አሁን በተፈጠረው እድል በዶሮ እርባታ ተሰማርቷል።
ማህበራቸው ከሚያመርተው ምርት ላይ በሚያገኘው ገቢ ከራሱ አልፎ ቤተሰብ እየደገፈ መሆኑን ነው የተናገረው።
የዲሬጠያራ ወረዳ ከዚህ በፊት የማይታወቀውን የአሳ ምርት በጓሯቸው በቆፈሩት የውሃ ጉድጓድ የዓሳ ጫጬት በማስገባት እያረቡ መሆኑን የሚናገሩት ደግሞ የወረዳው ነዋሪ አቶ ጀቦ ሙመድ ናቸው።
ከግብርና ባለሙያ በሚያገኙት ምክር መሠረት ውጤታማ ለመሆን በትኩረት እየሰሩ እንደሆነ አንስተዋል።
የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሮዛ ዑመር በበኩላቸው፥በክልሉ በከተማና በገጠር እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት መርሐግብር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አልፎ ገበያን በማረጋጋት ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ወጣቶችን በተለያዩ ማህበራት በማደራጀትና በቤተሰብ ደረጃ በመተግበር ውጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዚህም ዶሮ እና እንቁላል፣ማር፣ወተት፣አሳ እና የተለያዩ ምርቶች እየተመረቱ ሕዝቡን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ በርካታ ዜጎች ከተረጂነት ወጥተው ወደ አምራችነት መሸጋገራቸውን ተናግረዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025