የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ ኢንተርፕራይዞችን የተወዳዳሪነት አቅም ለማሳደግ የፖሊሲ ማዕቀፍ ተግባራዊ ተደርጓል

Apr 8, 2025

IDOPRESS

ሆሳዕና ፤መጋቢት 29/2017 (ኢዜአ)፡- የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን አቅም ለማሳደግ የማኑፋክቸሪንግ ፍኖተ ካርታና የፖሊሲ ማዕቀፍ ተግባራዊ መደረጉን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ገለጸ።

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አለባቸው ንጉሴ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በሀገር ኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው፡፡


ተቋሙ የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ውጤታማ ለማድረግ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ የፋይናንስ፣ የማምረቻና የመሸጫ ቦታን በማቅረብና በማስተዳደር ላይ እየተሰራ ነው፡፡

በአነስተኛና መካከለኛ ደረጃ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን የተወዳዳሪነት አቅም ለማሳደግ የማኑፋክቸሪንግ ልማት ፖሊሲ፣ ፍኖተ ካርታና የፖሊሲ ማዕቀፍ ተግባራዊ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ባለፉት ሰባት ዓመታት የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሻሻል በተሰራው ስራ 7 ሺህ 525 የአስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የሊዝ ፋይናንስ ብድር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

ተግባሩን አጠናክሮ በማስቀጠል በዘርፉ የላቀ እመርታ ለማስመዝገብ እንደሚሰራም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ በበኩላቸው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የሚደረገውን ጥረት እውን ለማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪውን ማስፋፋትና መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ክልሉ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶችን በማሳተፍ እየሰራ ነው ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልሉ፣ የዞንና ልዩ ወረዳ አመራሮችና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.