አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦ በሰመር ካምፕ እና በክህሎት ኢትዮጵያ መርኃ ግብር የተሰሩ የፈጠራ ውጤቶች የክህሎት ባንክ ተከፍቷል።
የክህሎት ባንኩን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል መርቀው ከፍተውታል።
በክህሎት ባንኩ የሚገኙት የፈጠራ ውጤቶች ባለፈው ዓመት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም እንዲሁም በዘንድሮ የክህሎት ኢትዮጵያ ተሳታፊዎች የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ናቸው።
ይህ በፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሚገኘው የክህሎት ባንክ የቴክኖሎጂ ባለቤቶችን የፈጠራ ምርቶችን መጠቀምና ማስመረት ከሚፈልጉ ደንበኞች ጋር የሚያገናኝ ነው መሆኑ ተገልጿል።
ባንኩ ለጎብኚዎች ክፍት ሲሆን የመንግስት እና የግል ሴክተሮች የፈጠራ ውጤቶችን በመጎብኘት እንዲመረትላቸው የሚፈልጓቸውን ምርት ትዕዛዝ መስጠት የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ መኖሩም ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለ21 ኢንተርፕራይዞች ያዘጋጀው የመስሪያ ቦታ ርክክብ ተደርጓል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025