የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መስክ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ

Apr 10, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦የህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መስክ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ ።


በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ሞላልኝ አስፋው ከህንዱ ፒኤችዲ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና ኬኤልጂ ግሩፕ ኦፍ ኢንዱስትሪስ ከተሰኘው አምራች ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሽሪ ሄርማንት ጃን ጋር ተወያይተዋል።


ውይይቱ የኢትዮጵያ እና ህንድ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው።


አምባሳደር ሞላልኝ የኢትዮጵያን ብዝሃ የኢንቨስትመንት እድሎች አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።


የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ያሉ አማራጮችን እንዲቃኝ ጥሪ አቅርበዋል።


ሽሪ ሄርማንት ጃን በምክር ቤቱ ስር ያሉ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው እ.አ.አ ጁን 2025 የንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።


ከ130 ሺህ በላይ አባላት ያሉት ፒኤችዲ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የህንድ ላኪዎችን የሚወክል ግዙፍ ተቋም መሆኑን በኒው ዴልሂ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።


ኬኤልጂ ግሩፕ ኦፍ ኢንዱስትሪስ በህንድ እና እስያ ግዙፍ የፕላስቲክ እና የፕላስቲክ ውጤቶች አምራች ኩባንያ ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.