አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ ስራዎች ድጋፍ ለማድረግ እንደሚሻ አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፥የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የስራ ኃላፊዎችን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በኩታ-ገጠም የግብርና ልማት ስራዎችን ማስፋፋት፣ በግብርናው ዘርፍ የስራ ዕድል ፈጠራን ማስፋትና ዘርፉን በቴክኖሎጂ በመደገፍ እንዲዘምንና ሳቢ እንዲሆን በማድረግ ወጣቶችን ወደ ዘርፉ እንዲገቡ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
እንዲሁም በግብርና ኢንቨስትመንት፣በገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት እና በሌሎች የግብርና ልማት ስራዎች ምርታማነትን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።
ሚኒስትሩ የግብርና ዘርፍ ስራን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን መንግስት ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረ አመልክተዋል።
የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የስራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025