አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 2/2017(ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ግብርናውን በማዘመንና ሜካናይዜሽንን በማስፋፋት አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን የክልሉ የግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን በዘርፉ ያለውን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ፤ አርሶ አደሩን ከተረጂነት በማላቀቅ ወደ ምርታማነት ማስገባትና ተጠቃሚነቱን ማሳደግ የግብርና ዘርፉ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትም ዘርፉን በማዘመን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የግብርና ኢንሼቲቮችን ቀርፆ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ክልሉ ግብርናውን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ግቡ አድርጎ በርካታ ተግባራትንም አከናውኗል።
በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የግብርና ሜካናይዜሽን ስራዎች ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ምርትን ከብክነት በጸዳ መልኩ በጥራትና በብዛት ለማምረትና ለመሰብሰብ ማስቻሉም ተመልክቷል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የክልሉ የግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ በሪሶ ፈይሳ እንዳሉት የግብርና አሰራርን በማዘመን ዘርፉ ኢኮኖሚውን በሚገባ እንዲደግፍ ለማድረግ እና አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ አስችሏል።
በዚህም ባለፉት ጊዜያት በተደረገው እንቅስቃሴ በክልሉ የሚበረታታ ውጤት የተገኘ ሲሆን ዘርፉን ለማዘመን የተሰጠው ትኩረት የበለጠ ይጠናከራል ብለዋል።
በክልሉ በስራ ላይ ከሚገኙ ትራክተሮች በተጨማሪ በተያዘው በጀት ዓመትም የግብርና ዘርፉን ማዘመን የሚያስችሉ ተጨማሪ የእርሻ ትራክተሮች ለአርሶ አደሩ በሰፊው እየቀረቡ ይገኛሉ ብለዋል።
አቶ በሪሶ እንዳሉት አርሶ አደሩ ከአሁን በፊት በበሬ በብዙ ድካም ከሩብ ሄክታር ያልበለጠ ያርስ እንደነበረ አስታውሰው በአሁኑ ጊዜ በትራክተር በቀን ከ5 እስከ 10 ሄክታር መሬት ማረስ መቻሉን ተናግረዋል።
በተለይም የግብርና ምርትን ከብክነት በጸዳ መልኩ በጥራትና በብዛት እንዲመረት በማስቻልና በተፈለገው ጊዜ በማቅረብ እጅግ ተስፋ ሰጪ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ የግብርና ሜካናይዜሽን ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታውሰዋል።
ወደ ፊትም የክልሉ መንግስት አርሶ አደሩ ከባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ ወጥቶ ግብርናውን በዘመናዊ መንገድ እንዲመራ የተጀመሩ ጥረቶች የበለጠ ይጠናከራሉ ብለዋል።
በዚህም ለአርሶ አደሮች፤ የተደራጁ ስራ ፈላጊ ወጣቶች፤ ለማህበራትና ዩኒየኖች የብድር አቅርቦት መመቻቱን አንስተው በትራክተሮቹ አያያዝና አጠቃቀምን በተመለከተ ድጋፍ እንደሚደረግም ጠቁመዋል።
የክልሉ መንግስት ከሰሞኑ 1 ሺህ 402 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች፣ ለማህበራት፣ ለዩኒየኖች እንዲሁም ለመሠረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት ማስረከቡ ይታወሳል።
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሰሞኑን በሻሸመኔ ከተማ 1 ሺህ 402 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች እና ለማህበራት በስተላለፉበት ወቅት በክልሉ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተደረጉ ማሻሻያዎች ውጤት እያመጡ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025