አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 4/2017(ኢዜአ)፦ በ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 160 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰውነት አየለ በሰጡት መግለጫ፥ ቢሮው የገቢ መሰብሰብ አቅሙን ለማሳደግ ባከናወናቸው ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶች ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
ከተማዋ ከምታመነጨው ኢኮኖሚ ተገቢውን ገቢ በመሰብሰብ የከተማ አስተዳደሩ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት የሚያደርገውን ጥረት ለማሳካት እየተጋ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 163 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 160 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል።
አገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ፣ ብልሹ አሰራሮችንና ሌብነትን ለመቅረፍ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሥራ በማስገባት የገቢ አሰባሰቡን እያሻሻለ መምጣቱንም ነው ያነሱት።
የዕዳ ክትትልና አስተዳደርን በማጠናከር በዘጠኝ ወራት ብቻ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ መሰብሰቡን አንስተው፥ የታክስ ስወራን ለመቀነስ እየተሰራ ነው ብለዋል።
አዲስ የኦዲት ጥናት አረጋጋጭ የስራ ክፍል በማደራጀት በኦዲተሮች የሚወሰኑ ውሳኔዎችን በድጋሚ ኦዲት በማድረግና የኦዲት ጥራት በማረጋገጥና ብልሹ አሰራሮችን በመቀነስ የከተማዋ ገቢ እንዲጨምር እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
የገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ የስነ ምግባር ጉድለትና ብልሹ አሰራር የፈጸሙ 12 አመራሮች እና 121 ፈጻሚዎች ላይ እርምጃ መውሰዱንም ገልጸዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025