የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ሞጆ ከተማን የቆዳ ኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ የወጣውን ስትራቴጂ መተግበር የሚያስችሉ ጥናቶች እየተደረጉ ነው -ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

Apr 14, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 4/2017 (ኢዜአ)፦ሞጆ ከተማን የቆዳ ኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ የወጣውን ስትራቴጂ መተግበር የሚያስችሉ ጥናቶች እየተደረጉ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሞጆ ከተማ የቆዳና ቆዳ ውጤቶችን ጥራትና ተወዳዳሪነት የሚያስጠብቁ መሰረተ ልማቶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በአጋር አካላት የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ በከተማዋ የተገነቡት ዘመናዊ ቄራ፣ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ምርምርና ማምረቻ ማዕከላት እንዲሁም የቆዳ ሳተላይት ቤተ-ሙከራ ናቸው።


የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ በሞጆ ከተማ በርካታ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ይገኛሉ።

ለእነዚህ ኢንዱስትሪዎች የጋራ ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃና ማጣሪያ ማዕከል በመገንባት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከተማዋን የቆዳ ኢንደስትሪ መዳረሻ ለማድረግ የአዋጭነትና የአካባቢ ተዕፅኖ ግምገማ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው ብለዋል።

በከተማዋ ዘመናዊ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ለዜጎች የስራ ዕድል ፈጠራና አገሪቷ የተሻለ ገቢ እንድታገኝ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።


የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አብዱላዚዝ ዳኦድ (ዶ/ር) በበኩላችው፤ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት አንዱ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ግብ ነው ብለዋል፡፡

የቆዳው ዘርፍ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ላይ የሚገኝ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡


የሞጆ ከተማ ከንቲባ ጋዛል ሀሹ በከተማዋ ከሚገኙ ከ300 በላይ ኢንዱስትሪዎች መካከል ግማሽ ያክሉ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህም በከተማዋ ከፍተኛ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ማስቻሉን ጠቁመዋል፡፡


የተባበሩት መንግስታት ኢንዱስትሪ ልማት (ዩኒዶ)የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አሬና ፓትሪአ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቆዳና ቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሻለ አቅም እንዳላት ገልጸዋል።

ይህን እምቅ አቅም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ደግፎ ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ምርት ለማግኘት ተቋማቸው የተለያዩ የቴክኒክ ድጋፎችን እያደረገ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.