አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 5/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማቱ መንገዶች ለሚፈለገው ዓላማ እንዲውሉ በማድረግ በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገልጿል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማቶችን፣ ብሔራዊ ቤተ-መንግስትንና አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡
በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሚኒስትር ዴዔታ አማካሪ ቶሎሳ ፉፋ(ዶ/ር) ጉብኝቱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወኑ መሰረተ ልማቶች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ናቸው።
በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ በመቀየርና ዘመናዊ አኗኗርን በማስረጽ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ያደረጉት ጉብኝትም በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ለመመልከት እድል የፈጠረ ነው ብለዋል።
በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የመንግስትን የመፈጸም አቅምና ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ከመሆናቸው ባሻገር ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆናቸውን አንስተዋል።
በጉብኝቱ የተመለከቷቸው ፕሮጀክቶች በአጭር ግዜ ውስጥ ግንባታቸው ተጠናቆ አገልገሎት መስጠት የጀመሩ መሆናቸው ደግሞ በእጅጉ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
በከተማዋ የኮሪደር ልማት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የተገነባ መሆኑ ለትራንስፖርት ዘርፉ ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዋናነት የኮሪደር ልማቱ መንገዶች ለታለመላቸው ዓላማ በማዋል ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ስትራቴጂ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ተናግረዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025