አዲስ አበባ ፤ሚያዚያ 8/2017(ኢዜአ):- ዝነኛው ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ በሩሲያ ሞስኮ በተካሄደው “ብራቮ አዋርድ” በተሰኘ የዓለም የክላሲካል ሙዚቃ አዋርድ በክላሲካል ሙዚቃ ዘርፍ ሽልማት አግኝቷል።
ስነ ስርዓቱ በሞስኮ ጥንታዊው ቦልሾል ቴአትር አዳራሽ ተከናውኗል።
በሽልማቱ ላይ የብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት ከሆኑት ሩሲያ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ህንድ፣ ሰርቢያ እና ቤላሩስ የተወጣጡ ታዋቂ ሙዚቀኞች፣ የሙዚቃ ባለሙያዎች፣ ደራሲዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና የዘርፉ ተዋንያን ተገኝተዋል።
በሁነቱ ላይ የታደሙት በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ (ዶ/ር) ለዝነኛው ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ ለተበረከተለት ሽልማት የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፒያኒስቱ ኢትዮጵያ ለሩሲያ ህዝብ በማስተዋወቅ ለተወጣው ሚና ያላቸውን አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
አምባሳደር ገነት የሽልማቱ አዘጋጆች ኢትዮጵያ ለሙዚቃ እና ለባህል ልውውጥ እያበረከተች ላለው አስተዋጽኦ ለሰጡት እውቅና ምስጋና ማቅረባቸውን በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025