የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራምን ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል

Apr 18, 2025

IDOPRESS

ጋምቤላ፤ሚያዝያ 9/2017 (ኢዜአ)፦በጋምቤላ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እያደረገ ያለው የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን( ዶ.ር) ገለፁ።


በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ለከተማው ተጠቃሚዎች ተጨማሪ የአካባቢ ልማት ስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።


የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ(ዶ/ር) በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት፥ የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮግራም ነው።


በክልሉ በሚገኙ ከተሞች የመስራት አቅም እያላቸው መነሻ ድጋፍ ያላገኙ ዜጎችን በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እደሚቀጥልም ገልፀዋል።


የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሳይመን ሙን (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ መንግስት በከተሞች ያለውን የድህነት ምጣኔ ለመቀነስና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።


ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም የተጠቃሚዎችን ኑሮ በዘላቂነት ከማሻሻል ባለፈ የከተማን ገጽታ በመገንባት ረገድ የላቀ አበርክቶ አለው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.