አሶሳ፤ ሚያዝያ 14/2017(ኢዜአ):- ያገኙትን የሥራ ዕድል በማሳደግ ውጤታማ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸውን በአሶሳ ከተማ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ዜጎች ተናገሩ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ በበኩሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ33 ሺህ 996 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጿል።
በአሶሳ ከተማ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎች ለኢዜአ እንደተናገሩት የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው አጭር ጊዜ ቢሆንም ያገኙትን የሥራ ዕድል በማሳደግ ውጤታማ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በከተማዋ 10 ሴቶችን በአባልነት የያዘው ራህመቴ፣ ጠይባ እና ጓደኞቻቸው የባልትና ውጤቶች አቅርቦት የባልትና ውጤቶችን በራሳቸው እያዘጋጁ ለገበያ ያቀርባሉ።
የማህበሩ ሰብሳቢ ወይዘሮ ራህመቴ ሹልኬ እንዳሉት ከዚህ በፊት ያለምንም ስራ ቤት እንደሚውሉ ገልፀው፥ አሁን ላይ ጥሩ ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ስራውን ከመጀመራቸው በፊት አስፈላጊውን የክህሎት ስልጠና ማግኘታቸውን የገለጹት ወይዘሮ ራህመቴ ከትርፍ ክፍፍል ይልቅ የማህበሩን የገቢ አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የማህበሩ ገንዘብ ያዥ ወይዘሮ እማዋይሽ አባተ በበኩላቸው ያገኙት የሥራ ዕድል ራሳቸውንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ለመቀየር መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ገልጸዋል።
የማህበሩ አባላት ዕቁብ በመጣል የቁጠባ ባህላቸውን እያሳደጉ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ሌላው በጣፋጭ ምግቦች ዝግጅት የተደራጁት እነ አብዱልናስር አቡዘድ እና ጓደኞቹ በአሶሳ ከተማ እየተለመደ የመጣውን "ባቅላባ" በማዘጋጀት ለተጠቃሚዎች እያቀረቡ መሆኑን የማህበሩ ሰብሳቢ አብዱልናስር አቡዘድ ተናግሯል።
በተለይም በሰርግ ወቅት ባቅላባ የበርካታ ደንበኞች ፍላጎት እየሆነ በመምጣቱ ጥሩ የገበያ እድል እንደሚከፈትላቸው አክሏል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም ሸንገል እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ውስጥ 33 ሺህ 996 ዜጎች ቋሚና ጊዜአዊ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል።
የሥራ ዕድሉ የተፈጠረውም በአገልግሎት ዘርፍ፣ በግብርናና ኢንዱስትሪ መሆኑን ጠቁመው፤ በተለይም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአሳ ምርት የፈጠረው ምቹ ሁኔታ በርካታ ዜጎች በዘርፉ እንዲሰማሩ አድርጓል ብለዋል።
ዜጎች ባገኙት የሥራ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊው የድጋፍ እና ክትትል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች የራሳቸውን ገቢ እንዲያሳድጉ በማድረግ በኩል የአሰራር ማሻሻያ መደረጉን ተናግረዋል።
ኮሌጆቹ የአካባቢውን ፀጋ በመጠቀም የተለያዩ ምርቶችን በማምረት ለገበያ እያቀረቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025