የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

አዲሱ የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ ምርታማነትን በማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው

Apr 24, 2025

IDOPRESS

መቀሌ፤ሚያዚያ 15/ 2017/(ኢዜአ)፦አዲሱ የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ ፖሊሲ ምርታማነትን በማሳደግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ገለጸ።


በጊዜያዊ አስተዳደሩ የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ እያሱ አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደተናገሩት በፖሊሲው ዙሪያ ለግብርና ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ተከታታይ ስልጠና እየተሰጠ ነው።


ከዚህ ቀደምም 1 ሺህ 500 ለሚሆኑ የግብርና ባለሙያዎች በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል።


አዲሱ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ በዋናነት የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ዓላማ ያለው በመሆኑ ፖሊሲው በክልሉ ተፈፃሚ እንዲሆን እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆናቸውን አስረድተዋል።


በክልሉ ያሉ የግብርና ባለሙያዎች እና የግል ባለሃብቶችን ጨምሮ ሌሎች በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት አዲሱን ፖሊሲ አውቀው እንዲያስፈፅሙ የተጀመረው ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።


ከፖሊሲው ቁልፍ መስኮች መካከል ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እና የገጠር መዋቅራዊ ሽግግርን ማረጋገጥ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ግብርናውን በማዘመን የግል ባለሃብቱን ተሳትፎ ማሳደግ ላይ መሰረታዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ተናግረዋል።


የግብርና ሚኒስቴርም በክልሉ ለዘርፉ እድገት እውን መሆን የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ገልፀው፥ ለዚህም ቢሮው የላቀ ምስጋና ያቀርባል ብለዋል።


በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ላዕላይ ቆራሮ ወረዳ የእርሻ ጽህፈት ቤት የግብርና ባለሙያ ወይዘሮ ምብራቅ ገብረመድህን በፖሊሲው ቁልፍ ስትራቴጂ ዙሪያ ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡


ስልጠናው ተጨማሪ አቅምና ግንዛቤ ይዘን በሙያችን አርሶ አደሩን ለመደገፍ ያግዘናል ብለዋል፡፡


ለአርሶ አደሩ የሚሰጡትን ሙያዊ ድጋፍ ለማሳደግ በፖሊሲውና ስትራቴጂው ዙሪያ ተከታታይ ስልጠና መሰጠቱ አስፈላጊ እንደሆነ የገለፁት ደግሞ የዚሁ ወረዳ የግብርና ባለሙያ አቶ ተክላይ ሞገስ ናቸው፡፡


በግብርና ስራ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣትና በተለይ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ሙያዊ ኃላፊነታችንን ለመወጣት የሚያስችለንን የአቅም ግንባታ ስልጠና ወስደናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.