ጂንካ ፤ሚያዚያ 15/2017 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ በየትኛውም መስፈርት የሀገርና ህዝብን ህልውና መሰረት ያደረገ ጥያቄ መሆኑ ተገለጸ።
በዓለም ላይ የባህር በር የሌላቸው አገራት በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት በሰጥቶ መቀበል መርህ እና ሌሎችም አማራጮች በስምምነት የባህር በር ተጠቃሚ መሆናቸው ይታወቃል።
በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊና አህጉራዊ ደረጃ ስምምነቶችን በማድረግ የባህር በር ተጠቃሚ በመሆን የጋራ ተጠቃሚነትን የእድገት አማራጭ ማድረግ የቻሉ አገራት በርካቶች ናቸው።
ለአብነትም አፍጋኒስታን ከፓኪስታን ጋር እንዲሁም የላቲን አሜሪካዋ ቦሊቪያ ከፔሩ ጋር በመስማማት የባህር በር ባለቤት መሆን ችለዋል።
ከቀይ ባህር በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት የነበረች ቢሆንም በታሪክ አጋጣሚ የቅርብ ተመልካች እንድትሆን ተደርጋለች።
በመሆኑም አሁን ላይ መንግስት ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት ይገባል የሚል ጠንካራ አቋም በመያዝ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱን አጠናክሮ መቀጠሉ ይታወቃል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ በየትኛውም መስፈርት የሀገርና ህዝብን ህልውና መሰረት ያደረገ ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በቅርበት እያለች አጥታ የቆየችውን የባህር በር ለማግኘት መንግስት እያደረገ ያለው የዲፕሎማሲ ጥረትም የሚደነቅ ነው ብለዋል።
በዩኒቨርሲቲው የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት መምህር ምስክር ከተማ፤ የኢትዮጵያ ባህር በር ጉዳይ ሳይነሳ በዝምታ ለበርካታ ዓመታት በዝምታ መቆየቱ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የዘነጋ ነበር ሲሉ አንስተዋል።
በመሆኑም ለውጡን ተከትሎ መንግስት የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ ነው ብሎ መነሳቱ ከምንም በላይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መቆሙን የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ የመንግስትን ጥረት ሁላችንም የማገዝና የመደገፍ ኃላፊነት አለብን ብለዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ የሚሻ በመሆኑ በተለይም ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦችና በማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጉዳዩን አጀንዳ አድርገው መያዝ ያለባቸው መሆኑን አንስተዋል።
በዩኒቨርሲቲው የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ክፍል ኃላፊና የታሪክ መምህሩ ወንድማገኝ ነጋሽ፤ ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ የባህር በር ማጣቷ ለሁላችንም ቁጭት ፈጥሮብን ቆይቷል ብለዋል።
በመሆኑም አሁን ላይ ጥያቄው መነሳቱ በየትኛውም መስፈርት የሀገርና የህዝብን ህልውና መሰረት ያደረገ ጥያቄ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ የትውልዱ መሆኑን አንስተው ለምላሹ መሳካት በጋራ ቆሞ መስራት የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ረገድ በተለይም ምሁራን፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ታዋቂና ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና የዳያስፖራ አባላት የሁልጊዜም ጥያቄያቸው አድርገው ሊይዙት ይገባል ብለዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025