ጭሮ ፤ሚያዝያ 16/2017 (ኢዜአ)፡-በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ከለማው መሬት ከ2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ሀቢብ አብዱልከሪም ለኢዜአ እንደገለጹት የስንዴ ምርቱ የተሰበሰበው በዞኑ 15 ወረዳዎች ከለማው ከ65 ሺህ 413 ሄክታር መሬት ላይ ነው፡፡
የምርት መጠኑም ባለፈው አመት ከተገኘው ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ብልጫ እንዳለው አመልክተው የተቀረው 414 ሄክታር መሬት ላይ ያለው ሰብል እስከተያዘው ወር መጨረሻ እንደሚሰበሰብ ጠቁመዋል፡፡
በዞኑ በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በ15 ወረዳዎች የሚገኙ ከ240 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውንም አስታውሰዋል።
የዞኑ አርሶ አደሮች በዩኒየኖቹ በኩል ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በቦኬ ወረዳ ቦኬ ሀሮ ዱዳ ቀበሌ አርሶ አደር ከድር ዩሱፍ እንዳሉት ከግማሽ ሄክታር በላይ ማሳ በበጋ መስኖ ስንዴ ካለሙት መሬት አብዛኛውን በመሰብሰብ 16 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸጥ እያገኙ ያለው ገቢ የምርት ማሳደጊያ ግብአቶችን በበቂ ሁኔታ ለመግዛት እንዳስቻላቸው የተናገሩት ደግሞ ሌላኛው የቀበሌው ነዋሪ አርሶ አደር አብዱል አዚዝ መሀመድ ናቸው፡፡
በቀጣይ በልማቱ በንቃት በመሳተፍ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025