የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በጉባኤው ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከተጠቀሱት ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ፦

Apr 27, 2025

IDOPRESS

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ያካሔደውን ጉባኤ መጠናቀቅ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ላይ ከኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከተጠቀሱት ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ፦

በያዝነው አመት አጠቃላይ ኢኮኖሚው በታቀደው መሠረት በ8 ነጥብ 4 በመቶ የሚያድግ መሆኑን የሥራ አስፈጻሚው ገምግሟል፡፡

ግብርና በ6 ነጥብ 1 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ በ12ነጥብ 8 በመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ በ12 በመቶ፣ ኮንስትራክሽን በ12 ነጥብ 3 በመቶ፣ አገልግሎት ደግሞ በ7 ነጥብ 1 በመቶ የሚያድጉ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡

ያለፉት 9 ወራት ጠቅላላ የመንግሥት ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ134 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡ የውጭ ብድር ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ ወርዷል፡፡

ወደ ውጭ ገበያ የሚቀርቡት ስድስት ዋና ዋና ምርቶች፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸሩ ከ82 በመቶ እስከ 386 በመቶ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡

በስንዴ፣ በሩዝ፣ በቡና፣ በሻይ ቅጠል እና በፍራፍሬ ምርቶች በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ለመውጣት እየተደረገ ያለው ትግል ፍሬ እያፈራ መሆኑን አይተናል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዝቅተኛ ኑሮ በሚኖሩ ወገኖች ላይ ጫና እንዳያሳድር አስፈላጊ የሆኑና የታቀዱ የድጋፍ መርሐ ግብሮች መከናወናቸውንም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መርምሯል፡፡

ለማዳበሪያ 62 ቢሊዮን ብር፣ ለሴፍቲኔት 41 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር፣ ለነዳጅ 60 ቢሊዮን ብር፣ ለመድኃኒት 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር፣ ለምግብ ዘይት 6 ነጥብ1 ቢሊዮን ብር፣ እንዲሁም ለደመወዝ 38 ነጥብ 4 ቢሊ ዮን ብር ድጎማ ተደርጓል፡፡

ባለፉት 9 ወራት ብቻ 344 ሺህ 790 የውጭ ሀገር ሕጋዊ የሥራ ዕድሎች እና ከ3 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድሎች ተፈጥረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.