አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 27/2017(ኢዜአ)፦የዘመናችን አርበኝነት የኢትዮጵያን የተሟላ ሉዓላዊነትና ብልፅግና ማረጋገጥ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን አራተኛውን አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ በይፋ አስጀምረዋል።
በመክፈቻ ንግግራቸውም ውድድሩ የማንነታችን መገለጫና የጀግንነታችን ማሳያ በሆነው 84ኛው የአርበኞች ታሪካዊ የድል ቀን መጀመሩ ቀኑን ድርብ ፋይዳ ያለው ያደርገዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ወራሪ ጠላትን መክተው ሉዓላዊነቷን ያስጠበቁ ጀግኖች አገር መሆኗን አውስተው፤ይህ የመጀመሪያው ዘመን አርበኝነት እንደሆነ ገልጸዋል።
የዚህ ዘመን ትውልድ ደግሞ ሉዓላዊነቷን ከማስጠበቅ በተጨማሪ ድህነትና ኋላ ቀርነትን በማሸነፍ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች አገር የመገንባት ኃላፊነት አለብን ነው ያሉት።
የዘመናችን አርበኞች መንታ አርበኝነትን የተቀዳጁ ናቸው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤በአንዱ በኩል የአገራቸውን ሉዓላዊነት፣ ነጻነትና ክብር ማስጠበቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በሌላ በኩል ድህነትንና ኋላ ቀርነትን በማሸነፍ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሆነ በመጥቀስ፤የመጀመሪያው ዘመን ዐርበኝነት ሙሉ የሚሆነው በሁለተኛው ዘመን አርበኝነት ነው ብለዋል።
የሁለተኛው ዘመን አርበኞች በክህሎት፣በብቃት እና በፈጠራ ሥራ ውስጥ መሆናቸውን ጠቅሰው፥ይህ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
የአገራት የለውጥ ጉዞ የሚወሰነው በሀብት ብዛት ሳይሆን ሀብትን በመጠቀም መሆኑን በመጥቀስ፤የአገርን ሀብት በሚገባ ለመጠቀም ደግሞ ክህሎት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
መንግሥት ፈጠራ እና የክህሎት ልማት ለኢትዮጵያ ፍቱን መዳኛዋ በመሆኑ አገራዊ አቅምን በመደመር እና ራሱን የቻለ ተቋም በማደራጀት ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል።
በዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል ነው ያሉት።
ለማሳያነትም በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ግብርናን የሚያዘምኑ፣ የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ የተመቸ እና ውጤታማ የሚያደርጉ፣ ዲጂታላይዜሽንን የሚያፋጥኑ ቴክኖሎጂዎችን እየፈጠሩ ብቁ ሙያተኞችንም እያፈሩ ነው ብለዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በየዓመቱ የሚያዘጋጃቸው የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ውድድሮች በፈጠራ የበሰሉ ብሩህ አእምሮዎችን፣ የተፍታቱ እጆችን፣ በክህሎታቸው የበቁ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችሉ መድረኮች መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች በፈጠራና ምርምር አገርን ወደ ብልጽግና እንዲያሸጋግሩ ማበረታታት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።
የውድድር መርኃ ግብሩ በተደመረ አቅም ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂና ምርምር ውጤቶችን ለማውጣት፣ ዘመኑ የፈጠራ በመሆኑ ኢትዮጵያን ወደ ልዕልና ለመውሰድ ያልተሞከረውን መሞከር፣መፍጠር እና መፍጠን አለብን ብለዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025