ጊምቢ፤ሚያዝያ 28/2017 (ኢዜአ)፦በምዕራብ ወለጋ ዞን በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ገለጸ።
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገቢዎች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገረመው ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች 2 ቢሊዮን 751 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል።
የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለውም ገልጸዋል።
በዞኑ የሰፈነው ሰላም በተለይም ለንግዱ ማህብረሰብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ ነጋዴው ግብሩን በአግባቡ እንዲከፍል ማስቻሉ ደግሞ ገቢው በዚህ ልክ ለመሰብሰቡ እንደዋነኛ ምክንያት ጠቅሰዋል።
እንዲሁም የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞችና አመራሮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ ባደረጉት ቅንጅታዊ ጥረት ገቢው ሊሰበሰብ መቻሉን ተናግረዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ የግብርና የታክስ ሕጎችን ተረድተው ግብራቸውን በጊዜ መክፈል እንዲችሉ በጽሕፈት ቤታቸዉ በተለያዩ ጊዜያት ስልጠናና የውይይት መድረኮች መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።
በተለይም በተያዘው በጀት ዓመት ግብር ከፋዮች በጊዜ እንዲስተናገዱ በቴክኖሎጂ የታገዘ የግብር አሰባሰብ ስርዓት መዘርጋቱን ሃላፊው አስረድተዋል።
የመንግስትን ታክስና ግብር በጊዜና በታማኝነት መክፈል የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ ያስችላል።
በመሆኑም ሁሉም ግብሩን በወቅቱና በታማኝነት በመክፍል የድርሻውን እንዲወጣ አቶ ገረመው አሳስበዋል፡፡
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025