የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ስድስተኛው ሴት የስራ ፈጣሪዎች የንግድ ትርዒትና ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ ተከፈተ

May 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2017(ኢዜአ)፦ 21 የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ(ኮሜሳ) አባል ሀገራት የሚሳተፉበት ስድስተኛው ሴት የስራ ፈጣሪዎች የንግድ ትርዒትና ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ ተከፍቷል።

የንግድ ትርዒቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ እና የአፍሪካ ህብረትና የኮሜሳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በይፋ አስጀምረዋል።

በስካይ ላይት ሆቴል የተከፈተው የንግድ ትርዒትና ኮንፍረንስ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

መርኃ ግብሩ ለኢትዮጵያውያን ሴት የስራ ፈጣሪዎች መነቃቃት የሚፈጥርና ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተመላክቷል፡፡

የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ(ኮሜሳ) 21 አባል ሀገራትን የሚያሳትፈው መርኃ ግብር አዳዲስና ትላልቅ የፈጠራ ሃሳቦችን ለማስተዋወቅና ለመጠቀም እንደሚረዳም ታምኖበታል፡፡

በንግድ ትርዒቱ ከ200 በላይ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ስራዎቻቸውንና ምርቶቻቸውን እንዳቀረቡ ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.