የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የግሉ ዘርፍ በመድኃኒት አቅርቦት ተሳትፎ እንዲጨምር አስችሏል

May 12, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 2/2017(ኢዜአ)፦የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የግሉ ዘርፍ በመድኃኒት አቅርቦት ላይ ያለውን ተሳትፎ እንዲያድግ ያስቻለ መሆኑን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ገለፀ።


ኢትዮጵያ ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራ መግባቷ ይታወቃል።


የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የውጭ ምንዛሬ መዛባትን ማስተካከልና የረጅም ጊዜ የውጭ ክፍያ ሚዛን ጉድለትን መፍታት፣ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፉን በማዘመን የዋጋ ንረትን መቀነስን ዓላማ ያደረገ ነው።


የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተለያዩ ዘርፎች ለውጦች እንዲመዘገቡ እያደረገ ይገኛል።


የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብድልቃድር ገልገሎ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከዚህ ቀደም በመድኃኒት አቅርቦት ዘርፍ ያለው የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ አነስተኛ ነበር።


የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ችግርን ለመፍታት የሚያስችልና የአምራቾችን ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ መሆኑን ተናግረዋል።


ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን በመግለፅ።


የአገር ውስጥ አቅራቢዎች ቁጥር ከፍ እያለ መምጣቱን ተናግረው፤ ይህም ኢትዮጵያ በራስ አቅም መድኃኒት የምታቀርብበት ስርዓት መፍጠር እያስቻለ ነው ብለዋል።


ተቋሙ የህግ ማሻሻያና የሪፎርም ስራዎችን እየተገበረ መምጣቱ ከመድኃኒት አቅርቦት ጋር የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት እድል እየፈጠረለት መሆኑን ተናግረዋል።


የመድኃኒት ፍላጎት ውል በተገባለት የአቅርቦት ስርዓት ለመምራት በተጀመረው ስራ ሳይቆራረጥ ለማቅረብ የሚያስችል የሶስት አመት ውል መገባቱንም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.