አዲስ አበባ፤ግንቦት 2/2017(ኢዜአ)፦ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያ በዘርፉ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች ያላቀ ቀሪዎቹን በብቃት ለመፈጸም ስንቅ የሚሆን ነው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡
ከሚያዚያ 27 ጀምሮ “ብሩህ አእምሮች በክህሎት የበቁ ዜጎች” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ የቆየው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ዛሬ ተጠናቋል፡፡
ውድድሩ በክህሎት፣በቴክኖሎጂና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዘርፎች ነው የተካሄደው።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ እንደገለጹት ፤ የክህሎት ልማት የሀገርን ተወዳዳሪነት ለመጨመር ወሳኝ ነው፡፡
የተካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያ በዘርፉ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች ያላቀ ቀሪዎቹን በብቃት መፈጸም የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን ማቅረብ የቻለ እና ገበያው የሚፈልገውን ቴክኖሎጂ ማበልጸግ ማስቻሉንም ገልጸዋል፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፥ ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
መርኃ ግብሩ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተወዳድረው አሸናፊ የሆኑ ወጣቶች የሚሳተፉበት የአሸናፊዎች አሸናፊ የክህሎትና የቴክኖሎጂ ውድድር መሆኑን አስታውቀዋል።
ውድድሩ የሰልጣኞችን ክህሎት በተግባር በመፈተሽ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ለኢንተርፕራይዞች በማሸጋገር ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ያስችላል ብለዋል።
በውድድሩ የአሸናፊዎች አሸናፊ ለሆኑ ክልሎች የወርቅ ዋንጫ፣ ሰርተፊኬትና የተሽከርካሪ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025