የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የክልሉ አመራር በየዘርፉ የተገኙ ድሎችን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መትጋት አለበት -ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

May 13, 2025

IDOPRESS

ቦንጋ፣ግንቦት 4 /2017 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አመራሩ በየዘርፉ የተገኙ ድሎችን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መትጋት እንዳለበት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።


"የመሐሉ ዘመን ወጥመድ መሻገር" በሚል መሪ ሀሳብ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።


ኢንጅነር ነጋሽ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፥ አመራሩ በየዘርፉ የተገኙ ድሎችን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መትጋት አለበት።


አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በማጠናከር ከህዝቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት እርካታ ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።


ሁልጊዜ አዳዲስ ሀሳቦችን በማፍለቅና ተግባራዊ በማድረግ ለተደማሪ ስኬት መትጋትና ውጤት ማስመዝገብ እንደሚያስፈልግ አንስተው፥ በዚህም የህብረተሰብን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ ጥረቱ መጠናከር አለበት ብለዋል።


የክልሉ አመራር በተለይም የኑሮ ዉድነትን ለማርገብና ስራ እድል ፈጠራን ለማጠናከር አቅሙን አሟጦ መጠቀም እንዳለበት አመልክተዋል።


የሚያጋጥሙ የመሐል ዘመን ፈተናዎችን በጽናት በመሻገር ወደ ብልጽግና የሚደረገውን ጉዞ ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ናቸው፡፡


የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ መቱ አኩ፣ ተግዳሮቶችን ለማለፍ ውጤት ላይ መሰረት አድርጎ መስራት እንደሚገባ አመልክተው፥ ለዚህም የልማት ኢንሼቲቮች ዉጤታማነትን ማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።


በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት የውስጥ አሰራር ላይ በማተኮር ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መረባረብ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.