ጂንካ፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፦ ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው የሚገኘውን ሀገራዊ ጥቅም ለማሳደግ በሳይንሳዊ ምርምር ማጎልበትና በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመደገፍ ማዘመን እንደሚገባ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።
በጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በቱሪዝም ላይ ያተኮረ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ ተካሂዷል።
በኮንፍረንሱ የምርምር ስራዎቻቸውን ያቀረቡ የዘርፉ ተመራማሪዎች ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው የሚገኘውን ሀገራዊ ጥቅም ለማሳደግ በሳይንሳዊ ምርምር ማጎልበትና በሰው ሰራሽ አስተውሎት መደገፍ ይገባል ብለዋል።
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የባህል ተመራማሪ ፕሮፌሰር ይስሃቅ ከቸሮ ቱሪዝምን በምርምርና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዘመን በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሑፍ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በቱሪዝም ሀብቷ ከፍተኛ አቅም ያላት ብትሆንም ከዘርፉ የሚገባትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እያገኘች አለመሆኑን ጠቁመዋል።
እንደ ኬኒያ ያሉ ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ከቱሪዝም ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ያሉት ተመራማሪው፤ ኢትዮጵያም ከዘርፉ ተገቢውን ጥቅም ለማግኘት የምርምር ውጤቶችን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በማቀናጀት መጠቀም እንዳለባት አመልክተዋል።
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፣ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ኢብራሂም ጀማል በበኩላቸው፤ የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማነቃቃትና ለማዘመን ሳይንሳዊ ምርምሮች ትልቅ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ቱሪዝም የዩኒቨርሲቲው ዋነኛ የትኩረት መስክ እንደሆነ ገልጸው፥ ዘርፉን በሳይንሳዊ ምርምር በማጎልበት ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው የሚገኘውን ሀብት ለማሳደግ ዩኒቨርሲቲው እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወይኒቱ መልኩ በበኩላቸው፥ በክልሉ ያሉ በርካታ የቱሪስት መስህቦችን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማሳደግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025