የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በኢትዮጵያ ይካሄዳል

May 16, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት 8/2017(ኢዜአ)፦ከ10 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙበትና በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ አለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።


ETEX 2025 ኤክስፖ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ አቅርቦት ጋር ተያይዞ በአለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያተረፉ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ነው።


በኤክስፖው ከፍተኛ ተቀባይነትና ዕውቅና ያላቸው ከመቶ በላይ የአገር ውስጥና የውጭ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ያስተዋውቃሉ።


በአዲስ አለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ዛሬ በይፋ በሚከፈተው የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ 10 ሺህ ተሳታፊዎች ይታደማሉ።


ኤክስፖውን ያዘጋጁት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሳይበር ደህንነት ተቋም ጋር በመተባበር ነው።


በኤክስፖው የአገር ውስጥና አለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ከማስተዋወቅ ባለፈ የተለያዩ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ።


የሳይበር ደህንነት፣አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ስማርቲ ሲቲና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን ጨምሮ የሮቦቲክስና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውድድሮች የሚካሄዱበት ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.