የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ኢትዮጵያ የልማት ግቦቿን ለማሳካት በምታደርገው ጥረት የአውሮፓ ሕብረት የልማት አጋሮች ድጋፍ ያደርጋሉ - አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገር

May 16, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የልማት ግቦቿን ለማሳካት በምታደርገው ጥረት የአውሮፓ ሕብረት የልማት አጋሮች ድጋፍ እንደሚያደርጉ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገር ገለጹ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ሕብረት ተወካይ ሌይላ ትራውሬ ፈርመውታል።

በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገር፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ተነሳሽነቶችን ይደግፋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በአውሮፓ ልማት ባንክ የተደረገው ስምምነትም የኢትዮጵያን ልማትና የፋይናንስ ሥርዓት መደገፍ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም የአውሮፓ ሕብረት የልማት አጋሮች ኢትዮጵያ የልማት ግቦቿን ለማሳካት ለምታደርገው ጥረት ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ፤ የመግባቢያ ስምምነቱ የሁለቱን ባንኮች ትብብር ለማጠናከር ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት መደገፍ የሚስችል መሆኑን ገልጸዋል።

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ሕብረት ተወካይ ሌይላ ትራውሬ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የስራ መሪነት ተግባራዊ የሚደረግ ነው ብለዋል።

በስምምነቱ መሰረትም ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚና ፋይናንስ ሥርዓትን ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት ድጋፍ የሚደረግ መሆኑንም አንስተዋል።

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ጄንስ ሀኔፌልድን፤ የጀርመን መንግስት በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም የሚደረጉ ጥረቶችን ይደግፋል ብለዋል።

ኢትዮጵያም አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ጀርመን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.